የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል በ42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር በቡድን ወጣት ወንዶች 3ኛ ደረጃን በመያዝ የ10,000 ብር ሽልማት ተበረከተለት።

ማዕከሉ ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው 42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ውድድር በ6 ኪሎ ሜትር ወጣት ሴት፣ 8 ኪ.ሜ ወጣት ወንዶችና በ8 ኪ.ሜ ድብልቅ ሪሌ ተወከሎ የውድድሩ ድምቀት በመሆን አጠናቋል።

በውድድሩም የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ ሙሀመድ ጃርሶን ጨምሮ የት/ት ስልጠና መሪ ስራ አስፈፃሚ ኢንስትራክተር ገረሙ ፈጠነ፣ አሰልጣኞች እና የቡድን መሪዎች በአዲስ አበባ ጃንሜዳ በመገኘት ቡድኑን አበረታተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *