📅 3 ጳጉሜን 2018 ዓ.ም. · ዓ.ም.
Tirunesh Dibaba Athletics Academy

የማዕከላችን ኮከቦች በ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ እና ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የሽልማት እጩነት ውስጥ በደመቀ ሁኔታ ተካተቱ!

1 ጳጉሜን 2018 ዓ.ም. · News
የማዕከላችን ኮከቦች በ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ እና ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የሽልማት እጩነት ውስጥ በደመቀ ሁኔታ ተካተቱ!Bronze Medal
የማዕከላችን ኮከቦች በ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ እና ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የሽልማት እጩነት ውስጥ በደመቀ ሁኔታ ተካተቱ! ************* ነሃሴ 30/2018 | በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የፊታችን ማክሰኞ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም በኢሊሊ ሆቴል በሚካሄደው የክበቦች የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ የማዕከላችን ተጫዋቾች እና አሰልጣኝ በበርካታ ዘርፎች በኮከብነት በዕጩነት ቀርበዋል። በ2018 የውድድር ዘመን ባሳዩት ድንቅ ብቃት እና አስደናቂ ተሳትፎ የሚከተሉት የማዕከላችን አባላት በእጩነት ተመርጠዋል፡ 👉 በኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ፡ # ኮከብ ተጫዋች እጩ፡ ሊዲያ ሰለሞን # ኮከብ ግብ ጠባቂ እጩ፡ ኢትዮጵያ ዳንግ # ኮከብ አሰልጣኝ እጩ፡ አሰልጣኝ ሰለሞን ገለታ 👉በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ፡ # ኮከብ ተጫዋች እጩ፡ ፀጋአብ ኤልያስ ስፖርተኞቻችን እና አሰልጣኛችን ለዚህ ትልቅ ስኬት እና የሽልማት እጩነት በመብቃታቸው ማዕከሉ የተሰማውን ታላቅ ደስታ እየገለጸ፣ በማክሰኞው የሽልማት ስነ-ስርዓት መልካም እድል እና አሸናፊነት ይመኛል!
← Back to News