የማዕከሉ ታዳጊዎች የሊጉን የበላይነት የሚያጸና ድንቅ ድል በፋሲል ከነማ ላይ ተቀዳጁ!

የካቲት 13/2018 | በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ (U-20) ዛሬ በተደረገ ተጠባቂ ጨዋታ ማዕከሉ የጎንደሩን ፋሲል ከነማን 6 ለ 2 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ድንቅ ብቃቱን አስመስክሯል።
በአሰልጣኝ ደረጄ ታመነ የሚሰለጥነው ቡድኑ ጨዋታው ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው በማዕከሉ የበላይነት የተመራ ሲሆን ተጫዋቾቻችን ሜዳው ላይ በነበራቸው ቅንጅት እና ግብ የማግባት ጥማት የፋሲልን ተከላካዮች የፈተነ ሲሆን በፈጣን መልሶ ማጥቃት እና ግሩም በሆኑ የኳስ ቅብብሎች የታጀበው የማዕከሉ እንቅስቃሴ ስድስት ግቦችን ለማስቆጠር አስችሏቸዋል።
ይህ ውጤት ቡድኑ በሊጉ ያለውን ጠንካራ ተፎካካሪነት ከማሳየቱም በላይ የወጣቶቹ ተስፋ ሰጪ ብቃት ለሰልጣኞቹ ትልቅ ደስታን የሰጠ ሲሆን ፋሲል ከነማዎች ሁለት ግቦችን ቢያስቆጥሩም የማዕከሉን የጥቃት ማዕበል መቋቋም ሳይችሉ ቀርተዋል።
ማዕከሉ ቀጣይ የ3ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ መርሃ ግብር የካቲት 17/2018 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ላይ ከወላይታ ዲቻ ጨዋታውን የሚያካሂድ ይሆናል።
⚽️ ጎል አግቢዎች
👉 23′ ናዝሬት ሰለሞን
👉 49′ አኑዋር ሙከዲስ
👉 59′ ግዛቱ ታረቀኝ
👉 70′ ኝዋኝ ጋትዶር
👉 74′ ዳዊት ፈጠነ
👉 82′ ፍሬቃል ሃይሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *