የቀድሞ የማዕከሉ ሰልጣኞች በ3000 ሜ. መሠናክል በአፍሪካ መድረክ ደመቁ!

ግንቦት 7/2018| በጋና መዲና አክራ እየተካሄደ በሚገኘው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የማዕከላችን ፍሬዎች የሆኑት የቀድሞ ሰልጣኝ አትሌቶቻችን የሀገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገው አውለብልበዋል።
ትላንት በተካሄደው የ3000 ሜትር መሠናክል ወንዶች የፍፃሜ ውድድር አትሌት ገመቹ ጎዳና ድንቅ ብቃቱን በማሳየት 1ኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበ ሲሆን አትሌት ሳሙኤል ፍሬው ብርቱ ፉክክር በማድረግ 3ኛ ደረጃን በመያዝ የነሃስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል።
ማዕከላችን ያስቀመጠው ጠንካራ መሰረት ዛሬ በአህጉር አቀፍ መድረክ ለሀገር ኩራት የሚሆኑ አትሌቶችን በማፍራት ውጤቱ እየታየ ይገኛል።
ሳይንሳዊ ስልጠና ቀጣይነት ላላው ተተኪ አትሌቶች “
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://atdatc.edu.et
Email: info@atdatc.edu.et

See less

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *