ማዕከሉ በወንዶች እግር ኳስ አቋም መለኪያ ጨዋታ ድል ቀናው!

ጥር 23/2018 | ትናንት ቅዳሜ ጠዋት 4:00 ሰዓት ላይ  በአዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሜዳ ላይ በተደረገ የወዳጅነት አቋም መለኪያ ጨዋታ፣ የማዕከሉ የ4ኛ ዓመት ወንዶች እግር ኳስ ቡድን የሸገር ሲቲ ከ20 ዓመት በታች (U-20) ቡድንን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

 

የማዕከሉ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን የቴክኒክ ብቃቱን ለመለካት ካደረጋቸው ተከታታይ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች መካከል ትናንት ቅዳሜ ከጠንካራው የሸገር ሲቲ ከ20 ዓመት በታች እግር ኳስ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ በድል አጠናቋል።

 

ቡድኑ በጨዋታው ላይ ከፍተኛ የሜዳ ላይ የበላይነት ማሳየት የቻለ ሲሆን፣ በተለይም በተጫዋቾቻችን መካከል የነበረው ቅንጅት እና ግብ የማግባት ብቃት የሚደነቅ ነበር። ይህ ውጤት ማዕከላችን እየሰጠ የሚገኘው ስልጠና ፍሬ እያፈራ መሆኑንና ተጫዋቾቻችንም በቀጣይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው ለኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ዝግጁ መሆናቸውን ያሳየ ነው።

 

የጎል አጋቢዎች፦

⚽️ ፍሬቃል

⚽️ ዳዊት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *